ሀብታሙ ግርማ ደምሴ (በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ረዳት ፕሮፌሰር)
ጥር 12 ቀን 2012 ዓ.ም

የጽሑፌን ርዕስ ተዋስኩት በአንድ ወቅት ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ አክራሪ የኢትዮጵያ ብሔርተኝነትን ለመንቀፍ የተጠቀመበት ሀረግ ነው፡፡ የዚህ ጽሑፍ ዓላማም አክራሪ ኢትዮጵያዊ ብሔርተኝነትን መንቀፍ ነው፡፡

ብሔርተኝነት ክፋት የለውም፤ አክራሪ ብሔርተኝነት ሲሆን ነው ችግሩ፡፡ አክራሪነት ጠንቁ ለራሱ ላከረረው ወገን ወይም ቡድን ነው፡፡ በኢትዮጵያ የአሁናዊ ገጽታዎች ዋነኛው አክራሪነት ነው፤ በብሔር አልያም በኢትዮጵያዊነት ጥላ ስር ቆመናል ብለው የፖለቲካ አጀንዳቸው ያደረጉ ሐይሎች በአክራሪነት ቀውስ ውስጥ ራሳቸውን ዘፍቀው፤ ራሳቸው ተቸግረው አገር እና ህዝብን እያስቸገሩ ነው፡፡

በሰሞኑ የጥምቀት በዓል ላይ ከተስተዋሉ ነገሮች አንዱ የባንዲራ ውዝግብ ጉዳይ ነው፡፡ እኔ እስከማውቀው ድረስ በስፋት ህዝብ ይዞት የሚወጣው ልሙጡ አረንጋዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ አርማም ሆነ ባንዲራ አይደለም ፤ ህጋዊ እውቅናም የለውም፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አርማም ይህ ባንዲራ አይደለም፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ ይፋዊ መለያ አረንጋዴ፣ ቢጫ፣ቀይ ሆኖ በመሃል አርማ ያለው ነው (ምስሉን ይመልከቱ)፡፡

በኢትዮጵያ የታሪክ ትርክት ሆነ የፖለቲካ አሰላለፎች እንደምናየው ልሙጡ ባንዲራ ያለፈው የጭቆና ስርዓት ምልክት እንደሆነ የሚያነሱ የብሔር ሆነ የሃይማኖት ማህበረሰብ ክፍሎች አሉ፡፡ ለአብዛኞቹ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች ይህን ባንዲራ ማውለብለብ ትርጉሙ ያለፈው ብሔራዊ ጭቆናን ማወደስ ነው፤ በለብዙሃኑ የእስልምና እንዲሁም የፕሮቴስታንት ክርስትና ተከታይ ኢትዮጵያዊንም ትርጉሙ እንዲሁ ነው፡፡

ኢትዮጵያ፤ ኢትዮጵያ የምንል ወገኖች የምር ኢትዮጵያን የምንፈልጋት ከሆነ በሌሎች ወንድሞቻችንን ቁስል ላይ ሌላ ህመም ባንጨምር ጥሩ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ቀናዒ ከሆንን ብዝሃነትን ማክበር አለብን፡፡ ይህ ካልሆነ ግን የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል እንዲሉ የምንጮኽላት ኢትዮጵያ ህልም ሆና ትቀራለች፤ ኢትዮጵያ ህልም ከሆነች ራዕያችን ሁሉ ህልም ሆኖ ይቀራል፡፡

አባቶች በደም እና በአጥንት ያስረከቡንን ውድ አገር እኛ ደግሞ በጭብጨባ እያፈረስን ለን አሳፋሪ ትውልዶች መሆናችን ያሳዝናል፡፡

ለአፍታም ቢሆን በአገር አልባነት ውስጥ የእያንዳንዳችን ህይወት ምን እንደሚመስል እናስብ፤ በፈረሰ አገር ውስጥ፡-
ስራ የለም! ቤተሰብ የለም! ልጅ ወልዶ መሳም የለም! መንፈሳዊ ህይወት የለም! ቤተ ክርስቲያን፣ መስጊድ የለም! ሳቅና ጨዋታ የለም! ደመወዝ የለም! ቢራ የለም! ጫት መቃም የለም! መስከርም ሆነ መመርቀን የለም! ጮማ መቁረጥ የለም! ወጥቶ መግባት የለም! ምንም የለም


Discover more from Habtamu Girma Demiessie (ሀብታሙ ግርማ ደምሴ)

Subscribe to get the latest posts to your email.

Published by Habtamu Girma Demiessie (ሀብታሙ ግርማ ደምሴ)

Habtamu Girma Demiessie is assistant professor of Economics at Jigjiga University, Ethiopia. An academic and a writer, Mr. Habtamu authored 8 books and published more than 85 scholarly works. His academic & literary works, which can be categorized as original research article, commentary, opinion or view point pieces, appeared on well read journals, Newsletters, print media and/or social media outlets in Ethiopia and abroad Readers interested to throw comments and/or critics on his works may contact the author via the following addresses: E-mail: • ruhe215@gmail.com • hab200517@yahoo.com Telephone (Mob): • +251 (0) 912 064 095. Website/Blog sites: •https://www.jigjigauniversity.academia.edu/HabtamuGirma •https://www.ruhehabtamu.wordpress.com/HabtamuGirma •https://www.researchgate.net/profile/Habtamu_Demiessie2

አስተያየት ያስቀምጡ

ይህ ጣቢያ አይፈለጌ መልዕክትን ለመቀነስ Akismet ይጠቀማል። የአስተያየትዎ ውሂብ እንዴት እንደሚሰናዳ ይወቁ

Discover more from Habtamu Girma Demiessie (ሀብታሙ ግርማ ደምሴ)

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading

Design a site like this with WordPress.com
ጀምር