የትግራይ ምርጫ ጉዳይ!

የትግራይ ምርጫ አሁንም ሆነ ዘግይቶ ቢካሄድ ውጤቱ አንድ ነው፤ ሂደቱ ላይ ነው ችግሩ። በሁለቱም ምርጫ ቢካሄድ ህወሓት እንደሚያሸንፍ የታወቀ ነው።
ነገር ግን የዛሬው ምርጫ ህገ መንግስታዊ መሰረት የሌለው እንደሆነ ይታወቃል። የእልህ አይነት ስለሆነ ምርጫው ምክንያትም፣ ውጤትም የለውም። ይልቅ ህወሓት ከእልህ ነቅቶ ለአገራዊው ምርጫ መዘጋጀት ይኖርበታል።

በቀጣዩ አገራዊ ምርጫ ውጤት ብልጽግና ትግራይ፣ ትዴፓ እና/ወይም ኣረና በክልሉ ምክር ቤት የየራሳቸው ወንበር/ድምጽ ይኖራቸዋል የሚል እምነት አለኝ፤ ስለዚህ እነርሱም ቢሆኑ ከእልህ ወጥተው ከህወሓት ጋራ የትግራይን ህዝብ በጋራ የሚያገለግሉበትን መንገድ መተለም አለባቸው።

Design a site like this with WordPress.com
ጀምር