እኛ ኢትዮጵያዊያን የአባይን ጉዳይ አሸንፈናል፤ አሁን የቀረን ራሳችንን ማሸነፍ ነው!

ኢትዮጵያዊያን ለዘመናት በአባይ ወንዝ ላይ ያለንን ቁጭት በብዙ መልኩ ስንገልጽ ኖረናል፤ አዝማሪው በድምጹ፤ ጸሐፍት በብዕራቸው፤ ተዋንያን በመድረክ ቴአትሮችና ፊልሞች እንዲሁም ምሁሩ በጥናትና ምርምሮቹ ስለአባይ ተክዘው ኖረዋል፤ እንደመታደል ሆኖ ይህ ትውልድ ከዚህ ትካዜ ለመላቀቅ የሚስችለውን አኩሪ ገድል ችግሮች ሳበግሩት አባይን በአገሩ አስሮ ለሃይል ማመንጫነት፣ ለአሳ ሃብት ልማት እንዲሁም ለቱሪዝም ወዘተ አውሎታል

አሁን የበረታብን ትልቁ ተግዳሮት ከራሳችን ጋር ያላቆምነው ጦርነት ነው፤ የዘመናችን የኢትዮጵያ ችግር እኛ ህዝቦቻ ራሳችንን ማሸነፍ አለመቻላችን ነው! ራስን ለማሸነፍ እንቅፋት ከሆኑብን ነገሮች ዋናው ስለጉዳዩ ያለን የተሳሳተ ግንዛቤ/አተያይ ነው፤ ለብዙዎቻችን ራስን ማሸነፍ መሸነፍ ነው፤ ራስን ማሸነፍ ደካማነት ነው፤ ነገር ግን ራስን ማሸነፍ ጀግንነት ነው፤ ሽንፈት ሳይሆን ድል ነው፤ ራሱን ያሸነፈ ከራሱ አልፎ በዙሪያው ላሉ ሁሉ መፍትሄ ይሆናል

እኛ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ያለንበትን ሁኔታ ከመረመርነው የችግሮቻችን ሁሉ መሰረት የሚሆነው ከራሳችን ጋር ጦርነት ውስጥ መግባታችን ነው፤ ራሳችንን አለማሸነፋችን ነው፤ ሁላችንም ደረጃው ወይም ፈርጁ ይለያይ እንጂ ከራሳችን ጋር ጦርነት ላይ ከከረምን ውለን አድረናል፤ በመሬት ላይ የምናየው የህዝብ ምስቅልቅል የፖለቲከኞች ቁማር እና/ወይም ዳፋ ብቻ አይደለም፤ እያንዳንዳችን ዛሬ ላለንበት አስከፊ ሁኔታ ድርሻ አለን

ይህ አጭር መጣጥፍ በሚከተሉት ነጥቦች ዙሪያ ዳሰሳ ያቀርባል፡-
• ለመሆኑ ራስን ማሸነፍ ምን ማለት ነው?
• ራሱን ያላሸነፈ ሰው ባህሪያት መገለጫዎች ምንድናቸው?

Design a site like this with WordPress.com
ጀምር