በኮሮና ቫይረስ ለእልቂት ከመዳረጋችን በፊት ስለበሽታው ያለንን የተዛባ አመለካከት ማስተካከል ግድ ይለናል!

የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገባ ከተባለ አስር ቀናት አለፉ፤ በእነዚህ ቀናት በስራ ምክንያት በተዘዋወርኩባቸው ድሬዳዋ፣ ሐረር እና ጅግጅጋ ከተሞች ህዝቡ ስለ በሽታው ያለውን አመለካከት ለመታዘብ እድሉ ነበረኝ፡፡

አብዛኛው ህዝብ የሚለው በሽታው ከጸሎት በቀር ምድራዊ በሆነ ነገር መጠንቀቅ አይቻልም ነው፤ ስለሆነም የፈጣሪ ቁጣ ነው፡፡ ለአንዳንዶቹ ደግሞ ከበሽታው ማምለጥ የማይቻልበት ምክንያት በአብዛኛው ህዝብ የቀን ገቢ ያለው በመሆኑ ኢኮኖሚያችን አንድ ቀን እንኳ ቤት እንድንውል አይፈቅድም የሚል ነው፡፡ ኢትዮጵያ የአምላክ የቃልኪዳን አገር ስለሆነች በሽታው እኛን አይመለከተንም የሚሉም በርካታ ናቸው።

በሽታውን የፈጣሪ ቁጣ አድርጎ በተስፋ መቁረጥ እጅ አጣጥፎ መጠበቁ አግባብ አይደለም፡፡ስለሆነም ወደ ፈጣሪ እጅን መዘርጋቱ መሰረታዊ መሆኑ ሳይዘነጋ፣ ነገር ግን አእምሯችንን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ ሁላችንም እንደየእምነታችን ጸሎት ማድረጉ ወሳኝ እንደሆነ አምናለሁ፤ ነገር ግን በህክምና ባለሙያዎች የሚሰጡ ምክሮችን ቸል ብሎ ጸሎት ማድረጉ አንዱን ይዞ አንዱን ጥሎ አይነት ነው፡፡

Design a site like this with WordPress.com
ጀምር